የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ከ 3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ

ዩኒቨርስቲው በመደበኛው፣ በቀንና በማታ እንዲሁም በክረምት መርሃ-ግብር በ2012 ዓ.ም ያስተማራቸውን፣ 2 ሺህ 376 ወንዶችን እና 1 ሺህ 336 ሴቶችን በድምሩ 3 ሺህ 712ተማሪዎችን በዛሬው እለት በሓዲስ አለማየሁ አዳራሽ አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው ያስመረቀው ለ13ተኛ ጊዜ ሲሆን ተማሪዎቹ በመጀመሪያና 2ተኛ ዲግሪ የተመረቁ ናቸው።

ዩኒቨርስቲው ከተመሰረተበት 2000 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ ከ40 ሺህ በላይ ተማሪዎችን አስተምሮ ለሀገር አበርክቷል።

በጅብሪል ሙሃመድ
ሐምሌ 17 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *