በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት በቦሌ አለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ ወደ አየር ማረፊያዉ የሚመጡ አዉሮፕላኖች ማረፍ እንደማይችሉ ተነገረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዳስታወቀዉ በአየር ማረፊያዉ ባለዉ እስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት አዉሮፕላኖች ማረፍ አይችሉም ብሏል፡፡

በመሆኑም ወደ አዲስ አበባ እየመጡ ያሉ አዉሮፕላኖች ከቦሌ አየር ማረፊያ ዉጭ ባሉት እንዲያርፉ ሲል አየር መንገዱ አስታዉቋል፡፡

አየር መንገዱ ለደህንነት ቅድሚያ ገልጾ ቦሌ ያለዉ የአየር ሁኔታ እስኪስተካከል ድረስ ሌሎች አማራጮችን እንዳዘጋጀም ይፋ አድርጓል፡፡

በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ያለዉ የአየር ሁኔታ ሲስተካከል መደበኛ አገልግሎቱን በፍጥነት እንደሚጀምርም ታዉቋል፡፡

የአየር ሁኔታዉን በመከታተል ለደንበኞቹ መረጃዎቸን በፍጥነት እንደሚያደርስም አየር መንገዱ ያስታወቀ ሲሆን በዚህ ምክንያት በረራቸዉ የተስተጓጎለባቸዉን መንገደኞች ይቅርታ ጠይቋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በአባቱ መረቀ
ሐምሌ 19 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.