የተቀመጠውን መመሪያ የሚጥስ የአውሮፕላን አብራሪም ሆነ ኦፕሬተር ለሚደርሰው አደጋ ሃላፊነት እንደሚወስድ የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ አስጠነቀቀ፡፡

ማንኛውም የአውሮፕላን አብራሪም ሆነ ኦፕሬተር የተቀመጠውን መመሪያ ጥሶ የሚንቀሳቀስ ከሆነ ለሚደርሰው አደጋ ሃላፊነት እንደሚወስድ የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ አሳስቧል፡፡

የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ በማህበራዊ ትስስስ ገጹ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ÷ ቀደም ሲል ሰኔ 23 ቀን 2013 ዓ.ም የአየር በረራ መረጃ ማሳወቂያ ማሳሳቢያ መስጠቱን አስታዉሷል፡፡

ቀደም ሲል ሰኔ 23 ቀን 2013 ዓ.ም የአየር በረራ መረጃ ማሳወቂያ (NOTAM& AIP SUP) ቁጥር A0166/21 እና AIP SUP A04 ,2021) መተላለፉን አስታውሷል፡፡

በተላለፈው መመሪያ መሠረትም ማንኛውም የአውሮፕላን አብራሪም ሆነ ኦፕሬተር የተቀመጠውን መመሪያ ከጣሰ ለሚደርሰው አደጋ ሃላፊነት የሚወስድ ይሆናል ነው ያለው፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 19 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *