ሊባኖሳዊው ቢሊየነር የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ::

ታዋቂው ባለፀጋ ናጂብ ሚካቲ ቀጣዩ የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መመረጣቸውን የአገሪቱ መንግስት አስታውቋል።

ሚካቲ በቀጣይ ከፕሬዚዳንት ሚሼል ኦውን ጋር በመሆን አዲስ መንግስት እንደሚመሰርቱም አልጄዚራ ዘግቧል።
ቢሊየነሩ በአሁኑ ሰዓት ትሪፖሊ እንደሚገኙ የተነገረ ሲሆን 72 ለ 42 በሆነ ውጤት አምባሳደር ናዋፍ ሳላምን ማሸነፋቸው ታውቋል።

በአገሪቱ በነበረው ተቃውሞ ምክንያት ጠቅላይ ሚኒስቶር ሳኣድ ሀሪሪ ከስልጣናቸው መሰናበታቸውን ተከትሎ ነው ሚካቲ በቦታው የተሾሙት።

ናጂብ ሚካቲ ከዚህ ቀደምም አገሪቱን በጊዚያዊነት ተረክበው መንግስት መመስረታቸው የሚታወስ ነው።

አልጀዚራ

በአባቱ መረቀ
ሐምሌ 20 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *