ህወሃት በአዲስ አበባ – ጅቡቲ መስመር ላይ ያሉ ሰብአዊ መተላለፊያዎችን ለማቋረጥ መሞከሩን ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ተናግረዋል።


“መንግስት በትግራይ ክልል የሚገኙ አርሶ አደሮች የዝናቡን ወቅት ተጠቅመው እንዲያርሱ በማለት የተናጥል የተኩስ አቁም ስምምነት ቢያደርግም በአሸባሪነት የተፈረጀው ሕወሃት ውሳኔውን ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ፣ በአዲስ አበባ – ጅቡቲ መስመር ላይ ያሉ ሰብአዊ መተላለፊያዎችን ለማቋረጥ መሞከሩን እና የሰሜን ምስራቁን የሀገሪቱን ክፍል ማጥቃቱን ተናግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ይህንን የተናገሩት ከተባበሩት መንግስታት የፖለቲካና የሰላም ግንባታ ጉዳዮች ምክትል ዋና ፀሀፊ ሮዜመሪ ዲ ዲካሎን ጋር በጽህፈት ቤታቸው በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡

በውይይቱ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን በትግራይ ጉዳይ ላይ ገለፃ አድርገዋል ተብሏል።

ዋና ፀሀፊዋ ዲካርሎ በበኩላቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተኩስ አቁም ስምምነቱ ውሳኔውን እንደሚደግፉ እና ሌላኛው ወገንም እርሱን እንዲከተል ያስፈልጋል ሲሉ መግለፃቸው ተነግሯል።

“ምንም እንኳን ሕወሃት መጥፎ ምግባሩን የቀጠለ እና ለመንግስት በጎ ፈቃድ አክብሮት እንደሌለው ያሳየ ቢሆንም አሁንም የኢትዮጵያ መንግስት ለተኩስ አቁም ስምምነት ቁርጠኛ ነው” ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማከላቸውም ተመላክቷል፡፡

ዋና ፀሀፊዋ የተባበሩት መንግስታት ኢትዮጵያ የቀጠናው ምሰሶ መሆኗን ይረዳል ማለታቸውን እና ይህንንም በመረዳት ግጭቶችን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለመፍታት መጣር ይገባል ሲሉ ማከላቸውንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 21 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.