ቦሌ አለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ ያለዉ የአየር ሁኔታ መሻሻል በማሳየቱ አዉሮፕላኖች ማረፍ መጀመራቸው ተነገረ

በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት ወደ አየር ማረፊያዉ የሚመጡ አዉሮፕላኖች ማረፍ እንደማይችሉ ባለፈዉ ሰኞ መነገሩ የሚታወስ ሲሆን ዛሬ ጠዋት ላይ አዉሮፕላኖቹ ማረፍ ጀምረዋል ተብሏል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዳረጋገጠዉ በቦሌ አለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ ተከስቶ የነበረዉ አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ መሻሻል በማሳየቱ ወደ አየር ማረፊያዉ የሚመጡ አዉሮፕላኖች ማረፍ መጀመራቸውን ገልጿል፡፡

ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ወደ ከቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ የሚበሩ አዉሮፕላኖች እያረፉ ሲሆን የአየር ሁኔታዉ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ሙሉ በሙሉ ይስተካከላል የሚል እምነት እንዳለዉ አየር መንገዱ አስታዉቋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በአባቱ መረቀ
ሐምሌ 21 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *