በሳውዲ አረቢያ የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸው ኢትዮጵያውን ጭምር እየታሰሩ ነው ተባለ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በአሁን ሰአት በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ ከ60 ሺህ በላይ ዜጎች በአሽቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ናቸው ።

በህገወጥ መንገድ ሳኡዲ የነበሩ ዜጎች ወደ አገራቸው የተመለሱ ቢሆንም አሁን ደግሞ የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ጭምር እየታሰሩ ነው ተብሏል፡፡

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ እየሰጡ ሲሆን በዚህ ወቅት እንዳሉት፣በሳውዲ በሚኖሩ ዜጎች አሁንም መታሰራቸውን ቀጥለዋል ብለዋል።

መንግስት በሳውዲ በችግር ላይ የሚገኙ 41 ሺህ 8 መቶ 73 ዜጎችን በአጭር ጊዜ ወደ አገራቸው መመለሱንም አምባሳደር ዲና አስታውቀዋል።

በቀጣይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በሳውዲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ለመርዳት በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

በተለያዩ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ በሚኖሩ ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን እንግልት መቃወማቸው ይታወሳል ።

ከሳውዲ የተመለሱ ዜጎችን ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑንም የሠላም ሚኒስቴር አስታውቋል።

የሠላም ሚኒስቴር የህግ ማስከበር ዳይሬክተር አቶ አሞባዬ ወልዴ በሰጡት መግለጫ ከሳውዲ የመጡት ዜጎችን ለማገዝ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ ነው።

የተመለሱ ዜጎች አብዛኞቹ ከትግራይ ክልል የሄዱ ሲሆን 13ሺህ በላይ ናቸው አማራ ሁለተኛ፣ ኦሮሚያ ደግሞ በሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

አባቱ መረቀ
ሐምሌ 22 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *