ቻይና የኑክሌር ሚሳኤልን የማከማቸትና የማስጀመር አቅሟን እያሰፋች መሆኗን የአሜሪካ ሳይንቲስቶች ተናገሩ ፡፡ 

በምዕራብ የሀገሪቱ ክፍል ምዕራባዊ ከምትገኘው ዢንጂያንግ የተገኙ የሳተላይት ምስሎች እንደሚሳዩት ቻይና የኒውክሌር ሚሳዔል ማብላያ ጣቢያ እየገነባች መሆኑን ይጠቁማሉ ሲል የአሜሪካ ሳይንቲስቶች ፌዴሬሽን (ኤፍ.ኤስ) አስታውቋል ፡፡

የአሜሪካ የመከላከያ ባለሥልጣናት በቻይና የኑክሌር ግንባታ ላይ ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል፡፡

ቻይና እየገነባች ያለችው ሁለተኛው አዲስ የኒውክሌር ሚሳዔል ማብላያ ጣብያ ግንባታው ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ በምዕራቡ ክፍል እንደተጀመረ ተነግሯል፡፡

ይህ ማብለያ ጣቢያ ከመሬት በታች የተገነቡና ሚሳዔል ለመተኮስ የሚረዱ 110 ማብላያዎችን ማቀፍ እንደሚችል ተነግሮለታል።

ባለፈው ወር ዋሺንግተን ፖስት የተሰኘው ጋዜጣ 120 ማብላያዎች ዩመን በተሰኘው የጋንሱ ግዛት በረሃማ ሥፍራ ታይተዋል ሲል መጻፉ የሚታወስ ነው፡፡

የሳይንቲስቶቹ ፌዴሬሽን ባለፈው ሰኞ ባወጣው ዘገባ ከዩመን 380 ኪሎ ሜትሮች ርቆ የሚገኘው አዲሱ ጣቢያ ግንባታው በቅርቡ የተጀመረ ነው ብሏል።

ባለፈው ዓመት ፔንታገን ቻይና የኒውክሌር ክምችቷን እጥፍ ለማድረግ እየሠራች ነው ሲል አሳውቆ ነበር፡፡

ቻይና ኒውክሌር ማብላያ ጣቢያ ይፋ የሆነው ፕላኔት በተሰኘው የሳተላይት ምስሎችን በሚሸጥ ድርጅት ሳቢያ ስለመሆኑ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር መቀመጫ ፔንታጎን ቻይና 200 የኒውክሌር መሣሪያ አሏት፤ እሱን እጥፍ ለማድረግ እየሠራች ነው ማለቱ የሚታወስ ነው፡፡

አሜሪካ 3800 ገደማ የኒውክሌር ሚሳዔሎች አሏት፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በያይኔአበባ ሻምበል
ሐምሌ 22 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.