እስራኤል በአፍሪካ ህብረት ታዛቢነት ቦታ እንድታገኝ መወሰኑ ደቡብ አፍሪካን አስቁጣ

የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ህብረቱ 55 አባል አገሮችን ሳያማክር ‹‹ የአንድ ወገን ›› ውሳኔ አሳልፏ ሲል ነው የከሰሰው፡፡

የአገሪቱ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ትብብር መምሪያ “ውሳኔው በፍልስጥኤም ጭቁን ህዝቦች ላይ የቦምብ ናዳ በወረደባቸው አመት መሆኑና መሬታቸው በህገወጥ በተወረረበት ወቅት መሆኑ የበለጠ አስደንጋጭ ያደርገዋል” ሲል አስታውቋል።

“እስራኤል የፈጸመቻቸው ኢ-ፍትሃዊ እርምጃዎች የአፍሪካ ህብረት የተቋቋመበት አላማና መንፈስን የሚጥስ ነው” መሆኑንም አክሏል፡፡

ደቡብ አፍሪካ ለአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃመት ለአባል አገራት ገለፃ እንድትሰጥ ትጠይቃለች ብሏል በመግለጫው።

የደቡብ አፍሪካው ተቃዋሚ ፓርቲ የኢኮኖሚ ነፃነት ታጋዮች (ኢ.ፌ.ኤፍ ) በበኩሉ የሊቀ መንበሩ ሙሳ ፋኪ መሃመት ውሳኔ አሳፋሪ እና “ በፍልስጥኤም ሰብአዊ መብቶች ላይ የተፈጸመ ጥቃት” በማለት ስልጣናቸውን እንዲለቁ ጥሪ አስተላልፏል።

እስራኤል በአፍሪካ አንድነት ድርጅት የታዛቢነት ቦታ የነበራት ቢሆንም ድርጅቱ በ2003 በአፍሪካ ህብረት ሲተካ የታዛቢነት ስፍራዋ አብቅቶ ነበር እንደ ቢቢሲ አፍሪካ ዘገባ።

ለአመታት ያህልም የታዛቢነት ስፍራ ለማግኘት የጣረችው እስራኤል በአንዳንድ የአፍሪካ ህብረት አባል አገራት ተቀባይነት በማጣቱ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በያይኔአበባ ሻምበል
ሐምሌ 22 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *