የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ድልድዮችንና ወታደራዊ ሰፈሮችን ለመገንባት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ።


የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ድልድዮችንና ወታደራዊ ሰፈሮችን በድንበር አካባቢ የጦር ሰፈር ለመገንባት እያደረገች ያለችው እንቅስቃሴ እያደረገች መሆኑን እና ይህ አይነቱ እንቅስቃሴ ስለማይጠቅማት ከድርጊቷ መቆጠብ አለባት ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ አስታወቁ፡፡

ኢትዮጵያ የድንበሩን ጉዳይ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ እያስረዳች መሆኑን የገለፁት አምባሳደር ዲና፣ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካይ ገለፃ ተደርጎላቸዋል ነው ያሉት።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በምክትል ፀሃፊነት የፖለቲካና የሠላም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ ሮዝመሪ ዲካርሎ ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገው በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ስለድንበር ጉዳዩ ገለፃ ተደርጎላቸዋል ተብሏል ።

ሃላፊዋም ድርጅቱ የኢትዮጵያን ጉዳይ በቅርበት እንደሚከታተለው መግለፃቸውን አምባሳደር ዲና አስታውሰዋል።

የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ከተቆጣጠረ ጀምሮ በርካታ ትንኮሳዎችን እያደረገ እንደሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን፣በአካባቢው የሚገኙ አርሶአደሮችም ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም ከምዕራብ ጎንደር ዞን ኃላፊዎች ሰምቷል ።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

አባቱ መረቀ
ሐምሌ 22 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.