የቻይና እና የካናዳ ካምፓኒዎች የኢትዮጵያን የቡና ስያሜዎች ለመከራየት ጥያቄ ማቅረባቸው ተነገረ፡፡

ባለፉት አምስት አመታት ኢትዮጵያ የቡና ስያሜዎቿን በአለም አቀፍ ደረጃ ለማስጠበቅ ከ30 በላይ ከሚሆኑ ሀገራት ጋር የውል ስምምነት ማድረጓ ይታወቃል፡፡

አሁን ላይ የውል ስምምነቱ መጠናቀቁን ተከትሎ በርካታ ሀገራት የቡና ስያሜዎቹን ለመከራየት ፍላጎት ማሳየታቸውን የኢትጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልጸዋል፡፡

የሀረር ፣የይርጋጨፌና የሲዳሞ ቡና ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያገኙ የሀገራችን የቡና ስያሜዎች ሲሆኑ ከ 30 በላይ በሚሆኑ ሀገራት በንግድ ምልክትነት መመዝገባቸውና የስያሜዎቹ ህጋዊ መብት እንዲጠበቅ መደረጉን ባላስልጣኑ አስታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቡናውን ወደ ውጭ ስትልክ የውል ስምምነቱን ለፈረሙት ብቻ መሸጥ ሲገባት የውል ፈራሚዎች ጥምረቱ እንዳይጠናከር በሚያደረግ መልኩ ቡና ገዥ ነኝ ብሎ ለሚመጣ ሁሉ ቡናው እየሸጠች ትገኛለች፡፡

በዚህም የኢትዮጵያ የአምራዊ ንብረት ጽህፈት ቤት ኢትዮጵያ በራሳ እጅ ውሉን ማፍረሷ ነው ያስታወቀው፡፡

ይህንንም ተከትሎ አለም አቀፍ ተቋማት የኢትዮጵያን የቡና ስሞች ለመከራየት ጥያቄ ያቀረቡት ተብሏል፡፡

በዚህም የቻይና እና የካናዳ ኩባንያዎች የኢትዮጵያን የቡና ስያሜዎች ለመከራየት ጥያቄ ማቅረባቸው ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

ሁለቱ ኩባንያዎች የኢትጵያን የቡና ስያሜዎች በየአምስት አመቱ በሚታደስ ውል መሰረት ነው ለመከራየት ጥያቄ ያቀረቡት፡፡

የኢትዮጵያን አለም አቀፍ የቡና የንገድ ምልክቶች ሊቆጣጠር የሚችል ተቋም እስካሁን ባለመቋቋሙ ሀገሪቷ በዘረፉ እየተጠቀመች እንዳልሆነ ነው የተነገረው፡፡

በአሥራ ሁለት ወራት ውስጥ 248 ሺኅ 311 ነጥብ 66 ቶን ቡና በመላክ 907 ነጥብ 4 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ትገኝቷል፡፡

በ2014 በጀት አመት በቡና ኤክስፖርት 280 ሺህ ቶን ቡና በመላክ አንድ ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት መታቀዱን ዶ/ር አዱኛ ተናግረዋል፡፡

ሐምሌ 22 ቀን 2013 ዓ.ም
ሔኖክ ወ/ገብርኤል

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *