“በአለት ላይ የተመሠረተው ኢትዮጵያዊነት ዛሬም ጠላቶቹን ያሸንፋል “ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ


የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ኢትዮጵያዊነት የተመሠረተው በአለት ላይ በመሆኑ ዛሬም የገጠሙንን ችግር እናሸንፋለን ብለዋል።

ሚኒስትሩ በጎንደር ዩንቨርስቲ የተማሪዎች የምርቃት መርሃ ግብር ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው ለተማሪዎች መልዕክት አስተላልፈዋል ።

”ጠላቶቻችን ኢትዮጵያ ትፈርሳለች ብለው ቢያሟርቱም እኛ ግን ጠላቶቻችንን አሳፍረንና አስደምመን ግድባችንን ሞልተናል አገራዊ ምርጫውንም በሰላም አከናውነናል ፤በቀጣይም አንድነታችንን አጠናክረን በአገር ውስጥ እና በውጭ ያሉ ጠላቶቻችንን ማሳፈር አለብን” ብለዋል ።

ጥራት ያለው ትምህርት አገርን በዕድገት ጎዳና ይመራል ያሉት ሚኒስትሩ ትምህርት ላይ አትኩረን በመስራት ለችግሮቻችን መፍትሄ ማምጣት ያስፈልጋል ።

ለዚህ ደግሞ ከትርክት ሴራ መውጣት እንደሚገባ ነው ኢንጂነሩ ያሳሰቡት።

ከዚህ በተጨማሪም ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ለክብር ዶክትሬት ተሸላሚው ለአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን የእንኳን ደስ ያለህ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ በቀጣይም በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ማዜሙን እንዲቀጥል ጠይቀዋል ።

የጎንደር ዩንቨርስቲ በዛሬው ዕለት 6 ሺህ 5መቶ 74 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

አባቱ መረቀ
ሐምሌ 24 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *