አሜሪካ በታሊባን ላይ የአየር ላይ ድብደባ መፈፀሟ ተሰምቷል።


የአሜሪካ ወታደሮች ከአፍጋኒስታን ምድር መውጣት መጀመራቸውን ተከትሎ በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሰው ታሊባን የተሰኘው ታጣቂ ቡድን ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ሲፈፅም ሰንብቷል።

የፓኪስታን ዜግነት ባላቸው ሰዎች እንደሚመራ የሚነገርለት ቡድኑ፣ በቅርቡ ለአፍጋኒስታን መንግስት ታላቅ የህልውና ጥያቄ ሆኖም ሰንብቷል።

በፈፀመው ተደጋጋሚ ጥቃትም በርካታ የመንግስት የፀጥታ አካለትን ጨምሮ በንፁህን ላይም ጥቃት ማድረሱ እንዲሁም ሚሊዮኖችን እንዲፈናቀሉ ማድረጉ ተገልጿል።

የታጣቂ ቡድኑ አባላት ከአፍጋኒስታን የመንግስት ሃይሎች ጋር ባደረጉት ፍልሚያ በማዕከላዊ መንግስቱ ስር ሲተዳደሩ የነበሩ ቁልፍ ቁልፍ ግዛቶችን በእጁ ማስገባቱም ተነገሯል።

ስለሆነም የአሜሪካ አይር ሃይል የታሊባን ይዞታዎች በሆኑ ቦታዎች ላይ ላለፉት 3 ቀናት የአየር ላይ ድብደባ መፈፀሙ ነው የተሰማው።

ወደ መዲናዋ ካቡል ለመግባት በሞከሩ እንዲሁም የታሊባን አባላት ይገኙበታል ተብለው በተጠረጠሩ ቦታዎች ሁሉ አሜሪካ እርምጃ መውሰዷም ተነግሯል።

የአሜሪካ መንግስት የአፍጋኒስታንን መንግስት ለመደገፍና የታሊባንን ጥቃት ለመመከት ትብብሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

የአሜሪካ ወታደሮች ወደ ሁለት አስርት የተጠጉ አመታትን በአፍጋኒስታን ከቆዩ በኋላ የጆ ባይደን አስተዳደር ከመጣ ወዲህ ወታደሮቹ እንዲወጡ መወሰኑ ይታወሳል።

አብዛኞቹ ወታደሮች የወጡ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ የመጪው ነሃሴ ወር ላይ ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በታሊባንና ማእከላዊ መንግሥቱ ግጭት ምክንያት በአፍጋኒስታን የፀጥታው ሁኔታ ከባድ እንደሆነ የሚነገር ሲሆን 3.5 ሚሊዮን ዜጎች ለስደት መዳረጋቸው ተገልጿል።

ሚድል ኢስት ሞኒተር

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ጂብሪል መሀመድ
ሐምሌ 27 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *