የሞሮኮ ንጉስ ፤ ከአልጄሪያ ጋር የሚዋሰኑትን ድንበር ክፍት እንዲሆን ጥሪ አቀረቡ

የሞሮኮ ንጉስ ሞሀመድ 6ኛ ፤ ለአልጄሪያ ወዳጅነት ጥሪ አቅርበዋል የምንዋሰነውን ድንበርም በድጋሚ ክፍት ማድረግ አለብን ብለዋል፡፡

ንጉሱ ይሄን ያሉት ፤ የዘውድ ቀን በመከበር ባለበት ሰአት ነው፡፡

እኛና አልጄሪያ አንድ ነን ያሉት ንጉሱ ፤ የአልጄሪያ ደህንነትና መረጋጋት ፤ የሞሮኮ ደህንነትና መረጋጋት ነው ፤ ምክንያቱም እኛ አንድ አካል ነን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እንደ አውሮፓውኑ ከ1994 ጀምሮ በአልጄርያና በሞሮኮ መካከል ያለው ድንበር ዝግ ነው፡፡

ሁለቱ ሀገራት በምዕራብ ሰሀራ ምክንያት የሻከረ ግንኙነት ነው ያላቸው ሞሮኮ ምዕራብ ሰሀራን የኔ ግዛት አካል ነው ትላለች፡፡

የቦታው ቀዳሚ ነዋሪዎች ሰሀራውያን ደግሞ ፤ስፔን ቦታውን ቅኝ ከምትገዛበት ጊዜ ጀምሮ ፖሊሳርዮ የተባለ ንቅናቄ አቋቁመው በሞሪታኒያ ሆነው ለነፃነት ሲታገሉ ኖረዋል፡፡

አልጄርያ ይሄን የፖሊሳርዮ ንቅናቄ ስለምትደግፍ ነው ከሞሮኮ ጋር ያላት ግንኙነት የሻከረው፡፡

ስፔን ምዕራብ ሰሀራን ስትለቅ፤ ሞሮኮና ሞሪታኒያ ቦታውን ተከፋፍለው የያዙ ሲሆን ሞሪታኒያ ሆኖ ይታገል የነበረው የፖሊሳርዮ ንቅናቄ፤ ወደ አልጄሪያ አቅንቶ በአልጄሪያ ድጋፍ ትግሉን ቀጥሏል፡፡

እንደ አውሮፓውያኑ ከ 1979 ጀምሮ ሞሪታኒያ ፤ በሰሀራ ቀደምት ነዋሪዎች ከተመሰረተው የፖሊሳርዮ ንቅናቄ ጋር ሰለም የመሰረተች ሲሆን ሞሮኮ ግን ሞሮታኒያ ይዛው የነበረውንም የምዕራብ ሰሀራ ክፍል ጠቅልላ ይዛለች፡፡

ራባት ተደጋጋሚ ድንበሩ ይከፈት ጥሪ ብታቀርብም ከአልጄርስ ምንም ቀና ምላሽ ተሰጥቷት አያውቅም፡፡

ይሄ የሞሮኮ ንጉስ ጥሪ የተሰማው ደግሞ በሁለቱ ሀገራት መካከል አዲስ ውጥረት በተፈጠረበት ሁኔታ ነው፡፡

ውጥረቱ ሞሮኮ የአልጄርያን ከፍተኛ የጦርና የፖለቲካ አመራሮች ሰልላለች የሚለው መረጃ ከወጣ በኋላ የመጣ ነው፡፡

የአልጄርያ መንግስት በሞሮኮ መንግስት የተደረገውን ስለላ ያወገዘ ሲሆን ከጎረቤት ሀገር ንጉስ የቀረበውን የድንበሩ ይከፈት ጥሪ ምላሽ አልሰጠበትም፡፡
ቢቢሲ

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በሔኖክ አስራት
ሐምሌ 27 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *