ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ ለማድረግ የሚያገለግል የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ተደረገ

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል Its My Dam የተሠኘ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ተደረገ።

የገቢ ማሰባሰቢያ መተግበሪያውን ወደ ሥራ ለማስገባት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አሸብር ባልቻ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚደንት አቶ አቤ ሳኖ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ እንደተናገሩት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ ሲሆን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ከፍተኛውን ወጭ በመሸፈን አጋርነቱን አሳይቷል ብለዋል፡፡

መተግበሪያዉ ከ1 ዶላር ጀምሮ እስከ 10 ሺህ ዶላር ድረስ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ሲሆን ይፋ የተደረገው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነው።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዘዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንዳሉት ገቢ ማሰባሰቢያ መተግበሪያው ግድቡን ለመጨረስ በሚደረገው ጥረት ድጋፍ ማድረግ ለሚፈልጉ ዳያስፖራዎች ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ብለዋል፡፡

መተግበሪያዉ ለግድቡ ድጋፍ ማድረግ ለሚፈልጉ በውጭ በውጭ ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በቀላሉ ድጋፍ እንዲያደርጉ ያግዛል፡፡

ከዚህ በፊት በውጭ ሀገር የሚገኙ ሰዎች ለግድቡ ድጋፍ ለማድረግ ሲቸገሩ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን www.Itsmydam.et የተሰኘው መተግበሪያ ይሄን ችግር በቀላሉ ይፈታል ተብሏል፡፡

ዲያስፖራው ለታላቁ የኤትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ እንዲያደርግ የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ዘዴዎችን ወደ ስራ የማስገባት ስራ እየተከናወነ ሲሆን ከቀናት በፊት www.mygerd.com የተሰኘ ድረገጽን መሰረት ያደረገ የድጋፍ ማሰባሰቢያ በይፋ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል፡፡

የሞባይል መተግበሪያው በይፋ ከመተዋወቁ አስቀድሞ በነበሩት 12 ቀናት 70 ሺህ ዶላር ለግድቡ ድጋፍ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በገቢ ማሰባሰቢያ መተግበሪያ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የሁለቱ ተቋማት የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፣ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አረጋዊ በርሄ እና የሌሎች ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 29 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.