የሀገር ውስጥ ዜና

በህወሃት ጥቃት ምክንያት ከ2 መቶ 20 ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸው ተነገረ፡፡

የሽብር ቡድኑ በአማራ እና በትግራይ ክልል በከፈተው ጥቃት ምክንያት ከ2መቶ 20ሺህ በላይ ዜጎች እንደተፈናቀሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታዉቋል።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በውቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ በመስጠት ላይ ሲሆኑን ፣በዚህ ወቅት እንዳሉት ህወሃት ዜጎችን እያፈናቀለ መሆኑን ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሳውቀናል ብልዋል ።

በተለይም ባለፈው ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ ለመጡት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች እና አስቸኳይ እርዳታ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ለማርቲን ግሪፍትስ በጉዳዩ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል ነው ያሉት።

በወቅቱም ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ለኃላፊው ህወሃት በዜጎች ላይ እያደረሰ ያለውን ጥቃት አስረድተዋል ተብሏል።

በተለይም ቡድኑ ዜጎችን እያፈናቀለ እያለ ድርጅቱ እና የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ዝም ማለቱ ተገቢ አለመሆኑም ተነስቷል።

ከዚህ በተጨማሪ ከሰሞኑ በተለያዩ አገራት ችግር ላይ የነበሩ 5 መቶ ዜጎች ወደ አገራቸው መመለሳቸውንም አምባሳደር ዲና በመግለጫቸው አንስተዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በአባቱ መረቀ
ሐምሌ 29 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *