በመርሳ ያሉ ተፈናቃዮች የወባ ስጋት እንዳለባቸው ተነገረ፡፡ 

አሸባሪው ህወሀት ከተቆጣጠራቸው ከራያ ቆቦ አላማጣና ዋጃ ተፈናቅለው 150ሺህ የሚደርሱ ተፈናቃዮች በወልዲያ እና መርሳ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

ከተፈናቃዮቹ ውስጥም በመርሳ የሚገኙት ዜጎች የወባ እና የኮሌራ ስጋት እንዳለባቸው የተፈናቃዮቹ አስተባባሪ የወልድያ ዩኒቨርሲቲ መምህር መንግስቱ አባተ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

የአማራ ክልል የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ስጋቱ እንዳለ አይተን የክልሉ ጤና ቢሮ አጎበሮችን እንዲያቀርብ መነገሩን በምክትል ኮሚሽነር እታገኝ አዳነ በኩል አሳውቋል፡፡

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የጤና አደጋ ጥናት ለማደረግ አጥኚ ቡድን መላኩንም ሰምተናል፡፡

ይሁን እንጂ ቡድኑ 8ሺ አጎበር ይዞ ቢሄድም ለተፈናቀዮች መስጠት አልቻለም ነዉ የተባለዉ፡፡

የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክተር አቶ አብርሀም አምሳሉ በአንድ ክፍል ውስጥ ከ 30 እስከ 40 ሰው ስለሚኖር አጎበር መዘርጋት እንዳልቻሉ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

የታቆረ ውሀ እንዳኖር ማድረግ፣ ሳር ማጨድና ትንኟ ልትራባ የምትችልበትን ቆሻሻ ቦታ ማጽዳት የሚለዉን እንደ መፍትሄ መወሰዳቸዉን ተናግረዋል፡፡

እናቶችና ህጻናትም በአካባቢው በሚገኙ ጤና ተቋማት ነጻ ህክምና እንዲያገኙ ማድረጋቸውንም አሳውቀዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በመቅደላዊት ደረጀ
ሐምሌ 29 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.