በ2014 ዓ.ም ስራ እንደሚጀምር የገለጸው ገዳ ባንክ በልማት ምክንያት ካሳ ተከፍሏቸው ለሚነሱ አርሶ አደሮችን የምክር አገልግሎት እንደሚሰጥ ገለጸ

በ2014 ዓ.ም ስራ እንደሚጀምር የገለጸው ገዳ ባንክ በዛሬው እለት የመስራቾች ጉባኤውን በአዲስ አበባ ሲያካሂድ እንዳስታወቀው፣ በልማት ምክንያት ካሳ ተከፍሏቸው የሚነሱ አርሶ አደሮችን የምክር አገልግሎት እንደሚሰጥ ገልጿል፡፡

የባንኩ አደራጅ ኮሚቴ አባል አቶ ሀምዲኖ ሚደቅሶ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ባንኩ ከ27 ሺህ በላይ መስራች ባለአክሲዮኖች እንዳሉትና በ2014 ዓ.ም ስራ እንደሚጀምር ነግረውናል፡፡

ባንኩ 1 ነጥብ 37 ቢሊዮን ብር የተፈረመ ካፒታል መጠን ያለው ሲሆን 550 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል እንዳለው ገልጸዋው፣ በአሁኑ ሠአት ስራ ለመጀመር የሚያስችለውን ህጋዊ ሂደቶች እየከወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አብዛኛው ለልማት ተብለው የሚነሱት አርሶ አደሮች የሚሰጣቸውን ካሳ በአግባቡ መጠቀም ላይ ክፍተት መኖሩን ያነሱት አቶ ሃምዲኖ፣ ባንኩ በ2014ዓ.ም ስራ ሲጀምር በልማት ምክንያት ካሳ ተከፍሏቸው የሚነሱ አርሶ አደሮችን የምክር አገልግሎት እንደሚሰጥ ይህም ለየት እንደሚያደርገው የባንኩ አደራጅ ኮሚቴ አባል ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

ገዳ ባንኩ ስራ ሲጀምር በትንሹ 15 ቅርንጫፎች ይኖሩታል ተብሏል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ረድኤት ገበየሁ
ሐምሌ 29 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *