የማይካድራዉ ጭፍጨፋ ሪፖርት አዲስ አበባ ለሚገኙ ዲፕሎማቶችና ለአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ሊቀርብ ነዉ

የህወሃት ቡድን በማይካድራ በዜጎች ላይ ያደረሰዉን ጥፋት የአለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲረዳዉ ለማድረግ በቅርቡ ለዲፕሎማቶችና ለመገናኛ ብዙሃን ሊቀርብ ስለመሆኑ ሰምተናል፡፡

የጎንደር ዩንቨርሲቲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀዉ የማይካድራን ጭፍጨፋ ሳይንሳዊ የምርምር ዘዴን ተከትሎ የተጠናዉ ጥናት ተጠናቋል ብሏል፡፡

የዩንቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ዶክተር አስራት አፀደወይን እንዳሉት ሪፖርቱ በአዲስ አበባ ለሚገኙ ዲፕሎማቶች፤ ሰባአዊ መብት ድርጅቶች ለአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን እና ለሌሎቸም የሚመለከታቸዉ ይቀርባል፡፡

በጥናቱ መሰረትም በማይካድራዉ ጭፍጨፋ ከ1ሺህ 6 መቶ በላይ ዜጎች እንደተገደሉ ታዉቋል፡፡

የዚህ ሪፖርት አላማ አለም እዉነታዉን እንዲረዳ ለማስቻልና በቀጣይ ልንማርበት የሚገባ አስከፊ የታሪካችን አካል እንደሆነም ፕሬዝዳቱ አስታዉቀዋል፡፡

የጥናቱ ውጤት እንደሚያመላክተዉ ከዘር ጭፍጨፋው በተጨማሪ በአካባቢው በሚኖሩ ህዝቦች ላይ ከፍተኛ የሆነ የቋንቋ፣ የባሕል፣ የጤና፣ የኢኮኖሚና የስነ-ልቦና ተጽእኖዎችና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መፈፀማቸዉንም ዶክተር አስራት ተናግረዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

አባቱ መረቀ
ሐምሌ 29 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *