ትናንትና ምሽት ላይ ህወሃት የተኮሳቸው ከባድ መሳሪዎች ወልድያ ከተማ በሚገኘው ሼክ ሁሴን መሐመድ አሊ አላሙዲን ስታዲዬም እና በሕዝብ መኖሪያ ቤቶች ላይ ማረፋቸው ተነገረ፡፡

የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ግዛቸው ሙሉነህ ዛሬም ጭምር በነበረው ተኩስ በርካታ ጉዳት መድረሱን አንስተው ዋና ዳይሬክተሩ በአማራ ክልል የሠሜን ወሎ ዞን አስተዳደር ዋና ከተማ በሆነችው የወልድያ ከተማ ከማታ ጀምሮ እስከ ዛሬ አራት ሰዓት ድረስ ከፍተኛ ውጊያ ሲደረግ እንደነበር ገልጸው፣ አሁን ላይ ግን የተወሰነ የተኩስ ፋታ መኖሩን ተናግረዋል፡፡

ወደ ወልዲያ ከተማ በተተኮሱ ከባድ መሳሪያዎች የደረሰው ዝርዝር ጉዳት እስካሁን ባለው ሁኔታ ባይገለጽም በንጹሃን ላይ ግን ጉዳት መድረሱን አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ለአል ዓይን ኒውስ ተናግረዋል፡፡

የህወሃት ቡድን ታጣቂዎች አሁን ላይ ይዟቸዋል ከተባሉት የአማራ ክልል አካባቢዎች ማስወጣት እንደ አንድ ተግባር ቢያዝም መንግስት ግን ቡድኑን እስከመጨረሻ ለማጥፋት “ቁርጠኛ” መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ነሐሴ 03 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *