የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከቱሉ ዲምቱ እስከ ቃሊቲ አደባባይ ድረስ የሚወስደው የ28 ኪሎ ሜትር የከባድ ውሃ መስመር የማዛወር ስራ በማከናውን ላይ መሆኑን አስታወቀ

ከአቃቂ እስከ ቃሊቲ ማሰልተኛ ድረስ በመንገድ ግንባታ ምክንያት ለሚቀየረው የውሃ መስመር 15 ኪ.ሜትሩ ባለ 800 ሚ.ሜ ስፋት ያለው ሲሆን ቀሪው 13.6 ኪ.ሜትሩ ደግሞ ከ125-400 ሚ.ሜ ስፋት ያለው ነው ብሏል ባለስልጣኑ።

ባለስልጣኑ እስካሁን 8.3 ኪሎ ሜትር የውሃ መስመር መቀየር የቻለ ሲሆን ለስራው የሚያስፈልገው ግብዓትም ተዘጋጅቷል።

መስመሮችን ለመቀየርም 66 ሚሊየን 680 ሺህ ብር ወጪ የሚፈጅ መሆኑን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ገልጿል፡፡

የመስመር ቅየራ ፕሮጀክቱን አሰር ኮንስትራክሽን አማካኝነት የሚከናወን ሲሆን እስከ ቀጣይ በጀት አመት ማብቂያ ድረስ ለማጠናቀቅ እየተሰራ የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታውቋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ነሐሴ 03 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *