ሳውዲ ዓረቢያ ለሁለት ሴቶች የከፍተኛ ሹመት ሰጠች 

ሳውዲ ዓረቢያ በሀገሪቱ የሚገኙ ሁለት ቅዱሳን መስጂዶችን በበላይነት እንዲያስተዳድሩ ለሁለቱ ሴቶች ስልጣን ሰጠች፡፡

ስልጣን የተሰጣቸው ሴቶች፤ አል-አኖውድ አል-አቦውድ እና ፋጢማህ አል-ረሺድ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

እዚህ ሴቶች በሃላፊነት እንዲያስተዳድሯቸው ሃላፊነት የተሰጣቸው ሁለቱ ቅዱሳን መስጂዶች፤ በሂጃዛ ክልል የሚገኙት፤ የመካው አል-ሀረም መስጂድና የነብያት መስጂድ ተብሎ የሚጠራው በመዲና የሚገኘው መስጅድ መሆናቸው ተነገሯል፡፡

ሴት ሃላፊዎቹ የሁለቱን ቅዱስ መስጂዶችን ጉዳይ የሚከታተለውን የፕሬዚደንቱን ጽ/ቤት አማካሪ በመሆንም ያለግላሉም ተብሏል፡፡

ሁለቱ ሴቶች የዶክትሬት ዲግሪ ያላቸው ሲሆን፤ ሌሎችም ሴቶች በተለያዩ አስተደዳራዊ ተቋማት ውስጥ ወደ ሃላፊነት እየመጡ መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡

በእስልምና ሃይማኖታዊ ስርዓት የምትመራው ሳውዲ ዓረቢያ፤ እስከ ቅርብ አመታት ድረስ በፖሊቲካዊ ጉዳዮች ዝቅተኛ የሴቶች ተሳትፎ የሚስተዋልባት ሀገር መሆኗ ይነገራል፡፡

በሳውዲ የሴቶች በተለያዩ ተቋማት ያላቸው የአመራርነት ሚና እ.ኤ.አ በ2018 ድረስ 22 ከመቶ ከነበረው በ2020 ደግሞ ወደ 33 መቶ ከፍ ማለቱን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ሳውዲ ዓረቢያ አሁን የሴቶችን በፖለቲዊ ጉዳዮች እንዳይሳተፉ አሳሪ የነበሩ ሃይማኖታዊ ህጎችን በማላላት የሴቶችን ተሳትፎ ለማሻሻል እየሰራች እንደምተገኝ የዘገበው አረብ ኒውስ ነው፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ጅብሪል መሐመድ
ነሐሴ 04 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.