የሀገር ውስጥ ዜና

በቀላል ባቡር እና በቀለበት መንገዶች ላይ ዘመናዊ የእግረኞች መሻገሪያ ድልድይ ሊገነባ ነው፡፡ 

በአዲስ አበባ ከተማ ቀላል ባቡር መንገዶች እና የቀለበት መንገድ ላይ የሚስተዋለውን የመንገድ ማቋረጫዎች ችግር ለመፍታት ዘመናዊ የእግረኞች መሻገሪያ ድልድይ ለማስገንባት በሂደት ላይ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ገለጸ፡፡

በድልድዮቹ የግንባታ ዲዛይን እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የኤጀንሲው አመራሮች እና የቻይናው ዥ ያንግ ዚ ዘ ሰከንድ ከተባለ የግንባታ ኩባንያ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

በከተማዋ በቀላል ባቡር መንገድ የሚጨናነቅባቸው ጉርድ ሾላ፣ መሪ ሲ ኤም ሲ እና ጎጃም በረንዳ እንዲሁም በአዲስ ሰፈር ሃኪም ማሞ በተባሉ አካባቢዎች የሚገነቡት ዘመናዊ የእግረኛ መሻገሪያ ድልድዮች ግንባታ የሚሆን ጥናት እና ዲዛይን ላይ ነው ውይይት ተደረጓል፡፡

የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ብርሃኑ ግርማ በከተማዋ የምስተዋለውን የትራፊክ ፍሰት በማቀላል እና የመንገድ ደህንነትን ማረጋገጥ ላይ ትኩረት ያደርጋል ብለዋል፡፡

እነዚህ ድልድዮች ከዚህ በፊት የተለያዩ አካባቢዎች ተገንብተው ሰው የማይጠቀምባቸው አይነት እንዳይሆን ተገቢው ትኩረት እንደተሰጠው ገልጸው አካል ጉዳተኞችንም ባማከለ መልኩ ምቹ ሆነው እንደሚሰሩ ኢ/ር ብርሃኑ አመልክተዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የቀረበው ጥናት ድልድዮቹ በሚገነቡባቸው ቦታዎች የመሬት አጠቃቀም፣ ወደ መንገዶቹ የሚወስዱ መጋቢ መንገዶች፣ የአውቶቡስ እና የታክሲ መጫኛ እና ማውረጃዎችን፣ የእግረኞች እንቅስቃሴን እና በአካባቢዎቹ የሚስተዋሉ የትራፊክ ፍሰቶችን መሰረት ያደረገ ነው ተብሏል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ነሐሴ 05 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *