ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ከረጅም ጊዜ እገዳ በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ በረራ ማድረጉ ተገለጸ፡፡


ከበረራ ችግር ጋር በተያያዘ ላለፉት ሁለት አመታት ያህል እገዳ ተጥሎበት የቆየው ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ከቻይናዋ ሻንጋይ ተነስቶ ወደ ደቡብ ምስራቅ አቅጣጫ በረራ ማድረጉን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ባለፈው ሳምንት ከአሜሪካዋ ሲያትል ተነስቶ ወደ ቻይና ለሙከራ እንዳመራም ነው የተገለጸው፡፡

የቦይንግ ኩባኒያ ዋና ሀላፊ ዴቭ ካልሁን እንደተናገሩት ኩባንያው የበረራ ፍቃድ ተሰጥቶት የነበረው ከአምስት ወራቶች በፊት ነበር ብለዋል፡፡

እስካሁንም በረራ ያልጀመረበት ምክንያት ማሟላት የነበረብንን ጉዳዮች ባለመጨረሳችን ምክንያት ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም በቅርቡ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ሙሉ አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል ብለዋል፡፡

ቦይንግ 737 ማክስ የኢትዮጵያ እና የማሌዢያ አደጋ አየርመንገዶች ላይ አደጋ ደርሶ 346 ያህል ሰዎች ህይወታቸው ካጡበት ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ ኪሳራ እንዳጋጠመው ተነግሯል፡፡

የሙከራ በራራው የተከናወነው በቻይና ከመሆኑ ጋር በተያያዘም ከፍተኛ ትችት እየተሰነዘረ መሆኑን እና ለዚህ ዋነኛ ምክንያት ደግሞ ሁለቱ ሀገራት በመካከላቸው የተፈጠረውን ንግድ ጦርነት መልስ ሳያገኝ በቻይና ሙከራ ማድረግ አልነበረበትም የሚል ነው፡፡

በአሁኑ ሰአት ቦይንግ ወደ ስራ መግባቱን ተከትሎ ከ175 በለይ የሚሆኑ ሀገራት አብረው ለመስራት ፍላጎት ማሳየታቸው አልጀዚራ አስነብቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ሔኖክ ወ/ ገብርኤል
ነሐሴ 05 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.