የአንድ መስኮት አገልግሎት በርካታ ተገልጋዮች በማግኘታቸው ከ39 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማዳን መቻሉን የገቢዎች ሚኒስቴር ገለፀ

ከ 64 ሺሀ በላይ አገልግሎት በአንድ መስኮት አገልግሎት በመስተናገዳቸው ከ 39 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጪ ምንዛሬ ማዳን መቻሉን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለጣቢያችን ገልጿል።

የአንድ መስኮት አገልግሎት የወረቀት አሰራርን የሚያስቀር መሆኑን ያስታወሰው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በገቢና ወጪ ንግድ የሚሳተፉ ተቋማትን በአንድ ላይ ያስተሳሰር የኤልክትሮኒክ አሰራር ነው ብሏል።

አገልግሎቱ በገቢና ወጪ ንግድ የተሰማሩ አካላት ባሉበት ሆነው ለተቆጣጣሪ መስሪያ ቤቶች ሰነዶችን በኤሌክትሮኒክ ለመላክ እና ለቢዝነስ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ነው ሲል ገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ የአንድ መስኮት አገልግሎት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በአንድ መስኮት አገልግሎት በተስተናገደ የገቢ ንግድ 64 ሺህ 604 ሲሆን የዉጭ ንግድ ደግሞ 5,097 ሆናል ብሏል።

በዚህም 39 ሚሊዮን 475 ሺህ 980 የአሜሪካ ዶላር ከብክነት ማዳን ተችሎኣል ብሏል።

በዚህ ስርዓት 14 ተቆጣጣሪ ተቋማት እንዲሁም 51 ባንኮችና ኢንሹራንሶች ተሳስረው አገልግሎት እንደሚሰጡ ሰምተናል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ሔኖክ አስራት
ነሐሴ 05 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.