የአፋር ክልል መንግስት ሽብረተኛ ተብሎ የተፈረጀው “ህወሓት” በፈንቲ ረሱ በጋሊኮማ ጊዚያዊ መጠለያ ተጠልለው የነበሩ በንፁሀን አርብቶ አደሮች ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ያለውን ጭፍጨፋ አስመልክቶ የሀዘን ቀን አወጀ። 

የአፋር ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ አሚና ሴኮ ይህን ጉዳይ አስመልክቶ በተጡት መግለጫ እንዳሉት ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የአፋር ክልል ባንዲራ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ የክልሉ መንግስት ወስኗል።

ህወሓት በጋሊኮማ በንፁሀን ላይ ያደረሰው ጭፍጨፋ እጅግ ዘግናኝ ነበር ያሉት አፈ ጉባኤዋ ፣ጥቃቱን ታሪክ የማይረሳው ነው ብለውታል፡፡

አፈ ጉባኤዋ “ህወሓት” ድንገት በከፈተው የከባድ መሳሪያ ጥቃት 107 ህፃናትን፣ 89 ሴቶችን እና 44 አዛውንቶችን ህይወት ተቀጥፏል፤ በርካቶች ተጎድተዋል፤ በመጋዝን የነበረ የአስቸኳይ እርዳታም ሙሉ በሙሉ ወድሟል ሲሉ አስታውሰዋል።

የተፈፀመውን ኢ ሰብአዊ ድርጊት ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በያሉበት ሆነው እንዲቃወሙና እንዲያወግዙ የክልሉ መንግስት ጥሪ አቅርቧል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ነሐሴ 05 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *