የአሜሪካ የደህንነት ተቋማት በአፍጋኒስታን የሚንቀሳቀሰው ታሊባን የተሰኘው ታጣቂ ቡድን መዲናዋን ካቡልን በ90 ቀናት ውስጥ በእጁ ሊያስገባ እንደሚችል አመላክተዋል፡፡
ነገር ግን የአፍጋኒስታን መንግስት ሀይሉን በማጠናከር ሊፈጥሩት ያሰቡትን ጦርነት ራሳቸውን እንዲጎዳ ማድረግ ይቻላል ተብሏል።
የአፍጋን መንግስት ጦሩን በካቡል እና ዙሪያዋን ባሉ ከተሞች ማስፈሩም እየተነገረ ነው።
ታሊባን እየሄደበት ያለው ፍጥነት ዋና ከተማዋን ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ እንዲቆጣጠር ያስችለዋል የሚለው የአሜሪካ የደህንነት ተቋም፣ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደንም የአሜሪካን ጦር አስወጥተው የአፍጋን መንግስት ብቻውን ጦርነቱን እንዲወጣው ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን አሳውቋል ኤ ኒውስ የተሰኘው የቱርክ ዜና ወኪል አስነብቧል።
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
መቅደላዊት ደረጀ
ነሐሴ 06 ቀን 2013 ዓ.ም











