“አሁን የአረንጓዴ አሻራ ብቻ ሳይሆን የደም አሻራም ያስፈልጋል “ሲል የኢትዮጵያ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን አስታወቀ


የህወሃት ሽብር ቡድን ከዚህ ቀደም እንዲህ አይነት የእብደት ተግባር ውስጥ ከመግባቱ በፊት ብዙ ቢለመንም አሻፈረኝ በማለቱ፣ ከእብድ ቡድን ጋር የሚደረግ ምንም ዓይነት ድርድር ሊኖር እንደማይችልና ቡድኑ አስታውቋል፡፡

የፐብሊክ ዲፕሎማሲ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጠ ሲሆን፣አሁን ላይ የአረንጓዴ አሻራ ብቻ ሳይሆን የደም አሻራም ያስፈልጋል ብሏል።

የህውሃት የሽብር ቡድኑ ጋር የሚደረግ ምንም አይነት ድርድር ሊኖር ስለማይችል፣ ይልቁንም ወደ ሲኦል እስኪወርድ ድረስ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እንደ አረንጓዴ አሻራ የደም አሻራውንም ማኖር ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡

የውጭ ሃይሎችም መንግስትንና የሽብር ቡድኑን እናስታርቅ ማለታቸው ተቀባይነት እንደሌለው ተነስቷል።

የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድኑ ከጎረቤት አገራት ጋር ያለንን ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰራም አስታውቋል።

በተለይም ከሱዳን ጋር ያለውን ወቅታዊ ግንኙነት በተመለከተ ውጥረቱን ለመቀነስ ወደ ሱዳን በማቅናት ውይይት ለማካሄድ ዕቅድ መያዙንም የኢትዮጵያ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድኑ አስታውቋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በአባቱ መረቀ
ነሐሴ 06 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *