“ሸኔን የወለደው ራሱ ሕውሃት ነው፤እርሱን ለመቃወም ነፍጥ ያነገተው ይህ ቡድን መልሱ የእርሱ ባሪያ መሆኑ ትግሉን ያለ አላማ መጀመሩን ያሳያል” የኦሮሞ ፓለቲከኞች

ሕውሃት የሚያደርሰውን ጫና ለመታገል ሲባል ከ2008 -2010 የተቋቋሙ ቡድኖች ፣ ዛሬ መልሰው ከዚህ አጥፊ የሽብር ቡድን ጋር ጥምረት መመስረታቸው በእጅጉ እንቆቅልሽ ነው ይላሉ ኢትዮ ኤፍ ኤም ያናገራቸው የኦሮሞ ፓለቲከኞች፡፡

በአቶ አራርሳ ቢቂላ የሚመራው የኦነግ ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ቀጀላ መርዳሳ ”እኔ እስከማውቀው ድረስ ህውሓትን ተቃውመው ወደ ጫካ የገቡት ወይም በሌላ መልኩ የሚንቀሳቀሱ ሰዎች ተመልሰው ከዚህ አሸባሪ ቡድን ጋር ግንኙነት ፈጥረናል ሲሉ ለኦሮሞ ህዝብም ሆነ ለኦሮሞ ነጻናት ግንባር እንቆቅልሽ ነው“ ይላሉ፡፡

እርግጥ ከዚህ ቀደም ይህ ነገር ሲነገር ስለነበር አዲስ አይደለም የሚሉት አቶ ቀጀላ፤ እነዚህ ሜዳ ሜዳውን የሚሉ ሰዎች ይህንን ስምምነት ያውቁታል ወይ ፤ተስማምተዋል ወይ የሚል ጥያቄ አለኝ ይላሉ ፡፡

”ምን አልባት እዚህ መሐል አዲስ አበባ ላይ ቁጭ ብለው ይህንን የወሰኑ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ ብዬ እገምታለሁ ”ሲሉ ያክላሉ፡፡

አቶ ቀጀላ እንደሚሉት ከዚህ በኃላ የነበረው የፓለቲካ መደበላለቅ እየጠራ መጥቷል፤ አሁን ማን ለሰፊው ህዝብ እንደቁመም ማሳያ ነውብለውዋል፡፡

የኦሮሞ ህዝብ ከማንም ጋር የማይለጠፍ የራሱን ጉዳይም ለማንም አሳልፉ የማይሰጥ ነው ብለዋል፡፡

ብሔርና ሀይማኖት ሳይለዩ ከጉምቱ ፓለቲከኞች ጨምሮ ከ600 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ጥብቅና የቆሙት የህግ ባለሞያ እና የቀድሞ የኦፌኮ አባል አቶ ወንድሙ ኢብሳ ”እኔ ይህንን ስሰማ ህውሃትን ሳይፈሩ ለህዝባቸው ራሳቸውን አስከወዲያኛው አሳልፈው የተሰው የኦሮሞ ልጆች ናቸው ድንቅ ያሉኝ “ይላሉ፡፡

“ከሀጫሉ ሁንዲሳ ጀምሮ ትህነግ የቀበረቻችው አንድ ሺህ የኦሮሞ ልጆች አጥንት ይፋረዳቸዋል ፤ይህ እጅግ አሳፋሪ ነው ”ይላሉ አቶ ወንድሙ፡፡

ሁሉም ፓለቲከኞች የኦሮሞን ስነ ልቡና እና የገዳ ባህልን እንዲያከብሩ እጠይቃለሁ ያሉት አቶ ወንድሙ ፤እነዚህ የኦሮሞም ሆነ የአማራ ፓለቲከኞች አንድም ለሀገራቸው፤ ሁለትም ለታሪካቸው ሲሉ ይህንን ጦርነት በድል ለማጠናቀቅ የዜግነት ድርሻቸውን ይወጡ ብለዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ያይኔአበባ ሻምበል

ነሐሴ 07 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *