ንብረትነቷ የፓናማ የሆነ መርከብ በሰሜናዊ ጃፓን ወደብ አቅራቢያ የመሰንጠቅ አደጋ ደረሰባት፡፡

ባለቤትነቱ የፓናማ የሆነ አንድ መርከብ በሰሜናዊ የጃፓን ወደብ አቅራቢያ መስመጧ ተሰምቷል፡፡
መርከቧ 39,910 ቶን የሚመዝን ጭነት ይዛ እንደነበር እና በደረሰባት አደጋ ለሁለት እንደተከፈለች ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

በአደጋው የነዳጅ መፍሰስ አደጋ ያጋጠማት ሲሆን በሰዓቱ በመርከቧ ውስጥ የነበሩ 21 ሠራተኞች ግን ምንም ጉዳት እንዳልደረሰባቸው ተነግሯል፡፡

ክሪምሶን ፖላሪስ የተሰኘችው ይህችው የፓናማ ባንዲራን ያነገበችው መርከብ ሄቻሄኖ በተሰኘው የጃፓን የወደብ ክልል ውስጥ ስትወድቅ የእንጨት ቁርጥራጦችን ጭና እንደነበር ተነግሯል፡፡

የአደጋው መንስኤ ምናልባትም መጥፎ የአየር ፀባይ ሊሆን እንደሚችል የተዘገበ ሲሆን መርከቧ ከወደቡ 4 ኪ.ሜ (2.4 ማይል) ያህል ርቀት ላይ እንቅስቃሴው ሊገታ ችሏል።

ጉዳት የደረሰባት የመርከቧ ሁለት ክፍሎች ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ ከስፍራው እንዳልተንቀሳቀሱና በቅርብ ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑን የአካባቢው የባህር ዳርቻ ጥበቃ ቃል አቀባይን ተናግረዋል ሲል ሮይርስ ዘግቧል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

የውልሰው ገዝሙ
ነሐሴ 07 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *