የደሴ ከተማ አስተዳደር ህገወጥ የዋጋ ጭማሪውን ለመቆጣጠር እየሰራ መሆኑን ገለጸ

ከሰሞኑ ከራያ አላማጣ ራያ ቆቦና ወልዲያ የተፈናቀሉ ዜጎች በደሴ ከተማ መጠለላቸው ይታወቃል።

በደሴ ከተማ ያሉ አንዳንድ ነጋዴዎችም የአልጋ ኪራይ ጨምሮ ምግብና ሌሎች ቁሳቁሶች ላይ ህገወጥ የዋጋ ጭማሪ ማድረጋቸው ሲነገር ቆይቷል።

ይህንንም ህገወጥ ድርጊት ግብረ ሀይል በማቋቋም ተቆጣጥረናል ሲሉ የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ አበበ ገብረመስቀል ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

ከንቲባው አክለውም በቁጥጥር ሂደቱ እርምጃ የተወሰደባቸው ንግድ ቤቶች እንዳሉ የነገሩን ሲሆን ዘላቂ መፍትሄ እንዲሆንም የአልጋ እና የምግብ ዋጋዎችም ተጽፈው በመግቢያ በር ላይ እንዲለጠፉ አድርገናል ብለዋል።

ከዚህ ውጪ የሚኖር የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ካለ ግን ተፈናቃዮችም ይሁኑ ሌሎች የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ቅሬታ እንዲያቀርቡ ነግረናል ሲሉ ገልጸዋል።

በደሴ ከተማ በአሁኑ ሰአት 60ሺ ተፈናቃዮች መኖራቸውን ሰምተናል።

ለተፈናቃዮች የውሀ አቅርቦት ችግር እንዳይፈጠር እዛው ባሉበት መጠለያ በውሀ ማጠራቀሚያ ታንከር እያቀረብን ነው ሲሉ ከንቲባው ነግረውናል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

መቅደላዊት ደረጀ
ነሐሴ 07 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *