ዴንማርክ እና ኖርዌይ በአፍጋኒስታን ያለውን ኤምባሲያቸውን ዘጉ፡፡ 

ታሊባን ካቡልን ለመቆጣጠር መቃረቡ ተከትሎ ዴንማርክ እና ኖርዌይ በአፍጋኒስታን ያለውን ኤምባሲያቸውን ዘግተዋል፡፡

የታሊባን ታጣቂ ቡድን የአፍጋኒስታን መዲና የሆነችውን ካቡል ለመቆጣጠር 80 ያህል ኪሎ ሜትሮች ብቻ ቀርተውታል።

ይህንንም ተከትሎ በርካታ ሀገራት ከሀገሪቱ ዜጎቻቸውን ለማስወጣት ጥረት እያደረጉ ነው፡፡

የአሜሪካ ወታደሮች ሀገሪቱን ለቀው መውጣታቸው ተከትሎ የታሊባን ሀይሎች በርካታ የአፍጋኒስታን ግዛቶችን በቁጥጥር ስራቸው አድርገዋል፡፡

አሁን ላይ የሀገሪቱ ዋና ከተማ የሆነችው እና በርካታ የውጭ ሀገራት ኤምባሲ የሚገኙባት ካቡልን ለመቆጣጠር መቃረቡ ተከትሎ፣ ኤምባሲዎች ለቀው እየወጡ ቢሆንም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግን በሀገሪቱ የሚገኙትን ሰራተኞቹ እንዳማያስወጣ ተናግሯል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይ የሆኑት ስቴፈን ጁጃሪች ከአፍጋኒስታን የሚወጣ አንድም ሰራተኛ የለንም ብለዋል፡፡

ዴንማርክ እና ኖርዌይ በአፍጋኒስታን ያለውን ኤምባሲያቸውን መዝጋታቸውን ሲያሳውቁ፣ እንግሊዝ እና አሜሪካ ግን ሰራተኞቻቸው እዛው እንደሚቆዩ አስታውቀው ኤምባሲያቸው እንደማይዘጉ ነው ያስታወቁት፡፡

የፔንታጎን ቃል አቀባይ ስቴፈን ኬርቢ ግን አሜሪካ በመጨረሻ ያልተጠበቀ ውሳኔ ሊታሳልፍ ትችላለች ብለዋል፡፡

አሜሪካ በአፍጋኒስታን የሚገኙትን ዜጎቿን ከሀገሪቷ ለማስወጣት 3ሺህ የሚጠጉ ወታደሮች በሳምንቱ መጨረሻ ወደ አፍጋኒስታን ልልክ ነው ብላለች፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ሔኖከ ወ/ገብርኤል
ነሐሴ 08 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *