በሀይቲ በተከሰተው ርዕደ መሬት የሟቾች ቁጥር 1ሺህ 300 ደረሰ፡፡

በተለያዩ ጊዜያቶች ርዕደ መሬት የማያጣት ሀይቲ አሁንም በዚሁ አደጋ የዜጎችን ህይወት ጠፍቷል፡፡

በሰሜን አሜሪካዊቷ ሀገር ሀይቲ በደረሰው ርዕደ መሬት እስካሁን ድረስ የሟቾች ቁጥር 1ሺህ 300 መድረሱ ሲነገር፣ ቁጥር ከዚህም በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል ተነግሯል፡፡

የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አደጋው በደረሰበት ቦታ የህይወት አድን ስራ እየሰሩ ሲሆን በርካቶች ከፍርስራሽ ስር እየወጡ ይገኛል ተብሏል፡፡

ከዚህ 7 ነጥብ 2 ሬክቴል ስኬል በሚለካው ርዕደ መሬቱ አሁን በሌሎች አካባቢዎች አደጋው ሊደርስ እንደሚችልም ተጠቁሟል፡፡

ከ11 አመት በፊት በዚህችው ሀገር ከፍተኛ መጠን ያለው ርዕደ መሬት መድረሱ አይዘነጋም፡፡

በዚህ አደጋ እስካሁን ድረስ ከ5ሺህ 700 በላይ ዜጎች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተነግሯል፡፡

ከወራቶች በፊት ፕሬዝዳንቷን የተገደለባት ሀይቲ በወራቶች ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ሀዘን ተቀምጣለች፡፡

ሀገሪቷ የፕሬዝዳንቱን መገደልን ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አውጃ ተግባራዊ እያደረገች በምትገኝበት ሰአት ነው አደጋው የደረሰው፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ነሐሴ 10 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *