በአዲስ አበባ በግንባታ ቦታዎች ላይ በደረሱት አደጋዎች ምክንያት የ23 ዜጎች ሕይወት ማለፉ ተነግሯል፡፡

የአዲስ አበባ ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በተጠናቀቀው በጀት አመት ከተሰበሰቡ 400 ያህል ጥቆማዎች 23 ያህል ዜጎች ሕይወታቸው ማጣታቸው ገልጿል፡፡

የቢሮ ምክትል የቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በከተማዋ ግንባታ የሚያካሄዱ ተቋራጭ ድርጅቶች እና ባለቤቶች ለሰራተኞቻቸው ተገቢውን ጥንቃቄ እያደረጉ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡

በዚህም በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በግንባታ ስራ ላይ በተሰማሩ ዜጎች ላይ የህይወት መጥፋት እና የአካል መጎዳት እየደረሰባቸው ይገኛል፡፡

ሀላፊዋ አክለው እንደተናገሩትም በከተማዋ ግንባታ በሚደረግባቸው ቦታዎች ተዟዙረው እንደተመለከቱት የግንባታ አካባቢዎች የጥንቃቄ ጉለት ይታይባቸዋል ብለዋል፡፡

ለዜጎቹ ሕይወት መጥፋት ዋነኛ ምክንያት የሆነው ለግንባታ የሚያስፈልጉ ጥንቃቄዎች ባለመደረጋቸው እንደሆነ ቢሮው አስታውቋል፡፡

የከተማው የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የሰራተኛውን መብት እንዲከበርለት የክትትል ስራ እየሰራ እንደሚገኝና የግንባታ ስራ የሚያከናውኑ ተቋራጮችም ሆኑ ባለቤቶች ግንባታ ከመጀመራቸው በፊት ለሰራተኞቻቸው የሚያስፈልገውን ግብአት ማሟላት የግድ ይላቸዋል ተብሏል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ነሃሴ 10 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.