ታሊባን ካቡልን በመቆጣጠሩ በሀገሪቱ በነገሰው ውጥረት የተነሳ የአፍጋኒስታን ዜጎች ቁጣቸውን በማህበራዊ ሚዲያ እና በተለያዩ አማራጮች ማሰማት ጀምረዋል፡፡
ላለፉት 20 አመታት ሀገሪቷን እንዳሻት ስታደርግ የነበረችው አሜሪካ በጭንቅ ሰአት ከአፍጋኒስታን መውጣቷ ግዴለሽነት ያሳያል ብለዋል፡፡
አሜሪካ ቀድማ ከአፍጋኒስታን ምድር የወጣች የታሊባን ግስጋሴ ስለተረዳች እና ለወታደሮቿ ስላሰበች ነው ይላሉ አፍጋኒስታናዊያን፡፡
አሜሪካ የራሷን ጥቅም ለማስከበር ላለፉት 20 አመታት የሀገሪቱን ዜጎች ስትጠቀምባቸው ነበር የሚሉት ዜጎቹ በጭንቅ ሰአት ዜጎቹን መመልከት ተስኗታል ብለዋል፡፡
አሜሪካ ላለፉት 20 አመታት በአፍጋኒስታን ስትቆይ በአስተርጓሚነት ያገለግሉ የነበሩትን የአፍጋኒስታን ዜግነት ያላቸው ዜጎች ወደ ዋሽንግተን የላከች ሲሆን እስካሁን ድረስም ወደ 2ሺህ የሚጠጉ ዜጎች ማቅናታቸው ነው የተሰማው፡፡
ታሊባን በትላንትናው እለት ዋና ከተማዋን ካቡልን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን ተከትሎ የሀገሪቱ መሪ የነበሩት አሽራፍ ጋኒ ከነ ቤተሰቦቻቸው ለጊዜው ወደ ኡዝቢኪስታን አቅንተዋል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ነሐሴ 10 ቀን 2013 ዓ.ም











