“የአማፂያንን የጦር አውርድ ለመግታት ዜጎች በጋራ መቆም ይኖርብናል” የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

መንግሥት ሁሉን አቀፍ «ብሔራዊ የሀገር ሉዓላዊነት እና የሕዝብ ደህንነት ማስከበሪያ ዘመቻ ግብረ ኃይል»እንዲያቋቁምም ኢዜማ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

አሁን ባለንበት ወቅት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በሕወሃት ጦረኝት በተለይ በጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በመከላከያ ሠራዊታችን ላይ በፈጸመው አስነዋሪ ድርጊት መነሻ የተፈጠረውን የሕግ ማስከበር የመንግሥት እርምጃን ተከትሎ የተፈጠረው ሰብዓዊ ቀውስ ሳይበቃ፤ ሕውሃት ወደ ሌሎች የሀገራችን ክፍል ለመስፋፋት በግልፅ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ብሏል፡፡

ለዚህም በቅርቡ ከኦነግ ሸኔ ጋር ያደረገው ይፋዊ ስምምነት የሚታወቅ ሲሆን ከሌሎች ተመሳሳይ ዕኩይ ተልዕኮ ካላቸው በሀገር ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ጋር ቀውሱን ለማስፋት እንደሚሠሩ በይፋ እየገለፁ ይገኛሉ ሲልም አክሏል፡፡

ሕወሃት ሀገራችንን ለማተራመስ ከሌሎች አክራሪ ብሔርተኞች ጋር ጥምረት መመስረት የሚችልበት ሁኔታ የሚፈጠር ከሆነ ለሀገራችን አንድነት እና ሰላም በራሱ ከሚፈጥረው አደጋ በተጨማሪ ለኢትዮጵያ የውጪ ጠላቶች መሣሪያ በመሆን በሀገራችን እና በምንገኝበት ቀጠና ከፍተኛ አደጋ ሊደቅን እንደሚችል አንስቶ የኢትዮጵያ አንድነት እና ሰላም እንዲረጋገጥ የምንፈልግ ኃይሎች በሙሉ አቅማችን ተረባርበን አደጋውን እንድንቀለብስ ከዚህ በፊትም ጥሪ አስተላልፈን ነበር ነው ያለው በመግለጫው።

ኢዜማ ችግሮች በኃይል አማራጭ ብቻ በዘለቄታው ይፈታሉ የሚል እምነት እንደሌለው አንስቷል

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ነሃሴ 10 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.