የዛምቢያ የምርጫ ኮሚሽን ተቃዋሚው ፕሬዝዳንታዊ ዕጩ ሀካይንዴ ሂኪሌማ ማሸነፋቸውን አረጋገጠ

በባለፈው ሳምንት በዛምቢያ በተካሄደ ፕሬዝዳታዊ ምርጫ ተቃዋሚው ፕሬዝዳንታዊ ዕጩ ሀካይንዴ ሂኪሌማ ማሸነፋቸውን የዛምቢያ የምርጫ ኮሚሽን አረጋገጧል፡፡

ሂኪሌማ ዋና ተፎካካሪያቸውን በስልጣን ላይ የሚገኙትን ኤድጋር ሉንጉ ያሸነፉት ከሚሊዮን በሚልቅ የድምፅ ብልጫ ነው፡፡

በስድስተኛ ሙከራቸው ነው ሂኪሌማ የተሳካላቸው ደጋፊዎቻቸው ድሉን በአደባባይ ወጥተው እያከበሩ ነው፡፡

ቀድሞ የኛ የምርጫ ታዛቢዎች ከምርጫ ጣቢያዎች ተባረዋል በሚል ፤ ምርጫው ነፃና ፍትሀዊ አይደለም ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበው የነበረ ቢሆንም በኋል ግን የ ኤድጋር ሉንጉ Patriotic Front ሽንፈቱን አምኖ ተቀብሏል፡፡

ለሂኪሌማም የእንኳን ደስ አሎት መልዕክት አስተላልፏል፡፡

በመጨረሻ ምርጫ ኮሚሽን ይፋ ባደረገው ውጤት መሰረት ሂኪሌማ 2 ሚሊዮን 810 ሺህ 777 ድምፅ ያገኙ ሲሆን በስልጣን ላይ የነበሩት ሉንጉ ደግሞ 1 ሚሊዮን 814 ሺህ 201 ድምፅ አግኝተው ተሸንፈዋል፡፡

ሂኪሌማ ቀጣዩ የዛምቢያ ፕሬዝዳንት መሆናቸውን የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር ኢሳዉ ቹሉ ይፋ አድርገዋል፡፡

የሉንጉ የ 6 አመታት አገዛዝ በሰብአዊ መብት ጥሰት፣ በሙስና፣ በደቀቀ ኢኮኖሚና በስራ አጥነት ሲተች ከርሟል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ሔኖክ አስራት
ነሐሴ 10 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *