ባይደን ከአፍጋኒሰታን የወጡበትን መንገድ ተከላከሉ፡፡ 

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በጦርነት ስትታመስ የነበረችዋን አፍጋኒስታንን ለታሊባን ለቀው የወጡበት መንገድ ከፍተኛ ትችት ገጥሞታል፡፡

‹‹ስንት አሜሪካውያን ህይወታቸውን መገበር ይገባቸዋል?›› ሲሉ ዲሞክራቱ ጆ ባይደን ጠይቀው ፤ ‹‹የአሜሪካ ወታደሮችን ከሀገሪቱ ለማስወጣት ከዚህ የተሻለ ጊዜ የለም ” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

አሜሪካ መራሹ ጦር ከአፍጋኒስታን የወጣበት መንገድ ችግር እንደነበረበት ያብራሩት ባይደን ‹‹አንድም የአሜሪካ ወታደር በአፍጋኒሰታን ምድር ሊሞት አይገባም ›› ብለዋል፡፡

በካቡል አየር ማረፊያ በርካታ ሰዎች አፍጋኒስታንን ለቀው ለመውጣት የአውሮፕላን ጎማ ላይ ሲንጠለጠሉ ታይተዋል፡፡

በአየር ማረፊያው ሰባት አፍጋኒስታናዊያን ህይወታቸው እንዳለፈ ተሰምቷል ፡፡

“አንድም የአሜሪካ ወታደር በአፍጋኒስታን መዋጋት የለበትም፣ መሞትም የለበትም፣ ያሉት ባይደን ፣የአፍጋኒስታን ወታደሮች ለማይዋጉለትና ለማይሞቱለት ጦርነት ለምን ብሎ አሜሪካዊ ወታደር ተዋግቶ ይሞታል?” ሲሉም ጠይቀዋል፡፡

በተቃራኒው ከ20 ዓመት በፊት የአሜሪካ ወታደሮች አፍጋኒስታንን እንዲወሩ ያደረጉት ጆርጅ ቡሽ በበኩላቸው ትዝብታቸውን ሲናገሩ ‹በአፍጋኒስታን እየሆነ ባለውን ነገር ታላቅ ሐዘን ይሰማኛል›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የህዝብ ሐሳብ መመዘኛዎች እንደሚጠቁሙት አብዛኛዎቹ አሜሪካዊያን በጆ ባይደን ውሳኔ ደስተኞች መሆናቸውን ሲገልጽ፣ የጀርመን መራሔተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ግን የምዕራባውያን ወታደሮች ከአፍጋኒስታን መውጣታቸው ኔቶ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ያጋጠመው “ትልቁ ውድቀት” ነው ሲሉም ተደምጠዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ነሐሴ 11 ቀን 2013
ያይኔአበባ ሻምበል

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.