አጣዬ ከተማ የጸጥታ ስጋት እንዳለባት ተነገረ፡፡

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የምትገኘው አጣዬ ከተማ፣ አሁንም የጸጥታ ስጋት እንዳለባት የከተማዋ ከንቲባ አቶ አገኘው መክቴ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

በ2013ዓ.ም ሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ ተባብሶ የተነሳው የኦነግ ሸኔ ጥቃት፣ ከ250ሺ በላይ የአጣዬና አካባቢዋ ነዋሪዎችን፣ ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሎ እንደነበር አይዘነጋም።

የአካባቢው ነዋሪዎችም አሁንም ቁስላቸው ሳይደርቅ አንዳንድ ትንኮሳዎች እየታዩ ነው ሲሉ ከንቲባው ለጣቢያችን ተናግረዋል።
የተለያዩ ትንኮሳዎች እንደሚስተዋሉ የነገሩን አቶ አገኘው የባለፈው አይነት ውድመት እንዳይፈጠር በራሳችን ማድረግ ያለብንን እያደረግን ነው ሲሉም ገልጸዋል።

አልፎ አልፎ ተኩሶች በማሰማት እና የብሄር ጉዳይ በማንሳት ህብረተሰቡን ለማሸበር መሞከርና መተንኮስ ይዘዋል ብለዋል፡፡
ከአጣዬ ከተማ ተፈናቅሎ የነበረው የአካባቢው ነዋሪ አብዛኛው የተመለሰ ሲሆን፣ ንብረቱን በማጣቱ ግን አሁንም በድህነት ውስጥ እንዳለ ነው የሰማነው።

ሱቆችና መሰል የንግድ እንቅስቃሴዎች ባለመኖራቸውም፣ ነዋሪው እርዳታ ለመጠበቅ መገደዱ ተገልጿል።
የጸጥታውን ስጋት በተመለከተ ከተማ አስተዳደሩ የሚችለውን እያደረገ ነው ያሉት ከንቲባው መንግስትም ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።

በመቅደላዊት ደረጄ
11 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.