በአዲስ አበባ የፓርኪንግ ቦታዎችንና የክፍያ መጠንን የሚያሳዩ ምልክቶች እየተተከሉ ነው::

በአዲስ አበባ የፓርኪንግ ቦታዎችንና የክፍያ መጠንን የሚያሳዩ ምልክቶች እየተተከሉ መሆኑን ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አሳወቀ::

በኮልፌ ቀራኒዮ እና ልደታ ክፍለ ከተሞች የፓርኪንግ ቦታዎች እና የክፍያ መጠንን የሚያሳዩ ምልክቶች በመተከል ላይ መሆናቸውን ኤጀንሲው ገልጿል::

የተተከሉት ምልክቶች በፓርኪንግ ማህበራት ተደራጅተው ከኤጀንሲው ጋር ውል በመግባት አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ማህበራት አገልግሎቱን የሚሰጡበት አካባቢን ለአሽከርካሪዎች የሚጠቁም ምልክት እና ለፓርኪንግ አገልግሎቱ የሚጠየቀውን የአገልግሎት ክፍያ ተመን የያዙ ናቸው።

በተለያዩ አካባቢዎች በፓርኪንግ አገልግሎት ተደራጅተው ከኤጀንሲው ጋር ውል የገቡ ማህበራት ከአሽከርካሪዎች የአገልግሎት ክፍያን ሲቀበሉ አሽከርካሪዎቹ የኤጀንሲው ስም እና ሎጎ ያለበት ደረሰኝ መቀበላቸውን ማረጋገጥ እንደሚኖርባቸው ከትራፊክ ማኔጅመት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል::

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ነሃሴ 12 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *