የተሽከርካሪ ዕግድ አገልግሎትን መቆሙን የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ፡፡

ብሔራዊ ባንክ ነሀሴ 6/2013 ዓ.ም ቤት፣መኪና፣ህንጻ እና ሌሎች ንብረቶችን በመያዣነት ተጠቅመው ብድር እንዳይሰጡ ለሁሉም ንግድ ለባንኮች መመሪያ ማውጣቱን ተከትሎ የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የተሽከርካሪ ዕግድ አገልግሎትን ማቆሙን አስታውቋል፡፡

በዚሁ መሰረት ተሽከርካሪዎቻቸውን በማስያዝ ከባንኮች ገንዘብ ተበድረው በአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ቅ/ፅ/ቤቶች ተሽከርካሪዎቻቸው እንዳይሸጥ ፣እንዳይለወጥ ለማሳገድ ተገልጋዮች እየቀረቡ እንደሆነ ገልጿል፡፡

ይሁን እንጂ በብሄራዊ ባንክ መመሪያው መሰረት ባለስልጣኑ የተሽከርካሪ ዕግድ አገልግሎትን መቆሙን አስታውቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን

ነሐሴ 12ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *