አዲስ አበባ ከተማ ቅርስ ጠል መሆኗን ቀጥላ በዛሬው እለት የራስ ሃይሉ ተክለሃይማኖትን መኖሪያ ቤት አፍርሳለች

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት የሚገኘው ራስ ኃይሉ ተክለሃይማኖት መኖሪያ ቤት በዛሬው እለት መፍረሱን የከተማው ባህል፣ቱሪዝም እና ኪነጥበብ ቢሮ ሃላፊ ተናግረዋል፡፡

ከከተማ አስተዳደሩ መቀመጫ በቅርብ ርቀት በሚገኘው ሰባራ ባቡር ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የሚገኘውን እና በቅርስነት የተመዘገበውን የራስ ኃይሉን መኖሪያ ቤት እያፈረሰ ያለው የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን መሆኑን የቢሮው ምክትል ሃላፊ ሰርጸ ፍሬ ስብሃት ለጣቢያችን አረጋግጠውልናል፡፡

አዲስ አበባ በአንድ በኩል እየገነባች በሌላ በኩል ደግሞ ጥንታዊ ቅርሶችን የምታፈርስ ከተማ መሆኑዋ እንዳሳዘናቸው የነገሩን ምክትል ቢሮ ሃላፊው ጉዳዩን ወደ ህግ እንደሚወስዱት ነግረውናል፡፡

የቤቶች ኮርፖሬሽን ከዚህ በፊት የአዲስ አበባ ታሪካዊ ቅርስ የነበረው ቡፌ ደላጋር ማፍረሱ ይታወሳል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በርካቶችን ያፈራው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የንግድ ስራ ትምህርት ቤት ወይም ኮሜርስ ለማፈረስ እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሚገኝ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ነሃሴ 18 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.