የደቡብና የሲዳማ ክልል ልዩ ሀይሎች የሰላም ማስፈን ስራቸውን በሚገባ እየተወጡ መሆናቸው በመተከል ዞን ለሰፈነው አንፃራዊ ሰላም አስዋፅኦው የጎላ ነው ተባለ

ወደ መተከል ዞን ድባጤና ሌሎች ወረዳዎች የአካባቢውን ሰላም ለመጠበቅ የተሰማራው የደቡብና የሲዳማ ክልል ልዩ ሀይል የዞኑን ሰላም እና ደህንነት በመጠበቅ አንጻራዊ ሰላም እንዲሰፍን የጎላ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሆነ የድባጤ ወረዳ ሰላም ፣ግንባታና ጸጥታ ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በመተከል ዞን የተለያዩ ወረዳዎች የጉሙዝ ሽፍቶች በርካታ ሰዎችን ህይወት ከማጥፋት እስከ ማፈናቀል ማድረሳቸው ይታወቃል።

ይህን ተከትሎ ክልሉ በኮማንድ ፖስት ስር መተዳደር ከጀመረ ወራት ማስቆጠሩ ይታወቃል፡፡

የህልውና ዘመቻ በተጠራው መሰረትም የሰላም ማከበሩን ሂደት ለማጠናከር ወደ መተከል ዞን ድባጤና ሌሎች ወረዳዎች ያቀናው የደቡብና የሲዳማ ክልል ልዩ ሀይል ከመከላከያ ሰራዊትና ከሚሊሻው ጋር በመሆን የሰላም ማስፈን ስራውን እየሰራ ነው ሲሉ የድባጤ ወረዳ ሰላም ፣ግንባታና ጸጥታ ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሀይማኖት ጎበና ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።

የመተከል ዞን በአሁኑ ጊዜ አንጻራዊ ሰላም አለ የተባለ ሲሆን የአካባቢው አርሶ አደርም እንደከዚህ ቀደሙ ባይሆንመ የእርሻ ስራቸውን እያከናወኑ እንደሆነ ሃላፊው ተናግረዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

መቅደላዊት ደረጄ
ነሃሴ 18 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *