ከአፍጋኒስታን እንዲወጡ የተደረጉ 51 ሰዎችን የያዘው የመጀመሪያ ቡድን ኡጋንዳ ደርሷል፡፡

ኡጋንዳ በአሜሪካ መንግሥት ጥያቄ 2,000 የአፍጋኒስታን ስደተኞችን ለመቀበል በተስማማችው መሰረት የመጀመሪያ ዙር ስደተኞችን የያዘው ቡድን ዛሬ ጠዋት ኢንቴቤ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መድረሱን የኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት አስታውቋል፡፡

ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ እንዳለው እነኚህ አፍጋኒስታናዊያን በኡጋንዳ ቆይተው ወደ አሜሪካ እና ወደ ሌሎች አገራት እንደሚሄዱ የገልጹ ሲሆን፣ስደተኞቹ በኡጋንዳ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቁዩ ግን ግልፅ አለመደረጉን ቢሲሲ አፍሪካ ዘገቧል ።

አፍጋናውያን ስደተኞቹ የኮቪድ -19 ምርመራ ያደረጉ ወንዶችን ፣ ሴቶችን እና ሕፃናትን ያካተቱ ሲሆን በገለልተኛነት እንደሚቀመጡ መግለጫው አስታውቋል።

ታሊባን አፍጋኒስታንን ከተቆጣጠረ ወዲህ የበቀል እርምጃውን በመፍራት በሺዎች የሚቁጠሩ ዜጎች ሀገሪቱን ለመልቀቅ እየተሰደዱ ነው፡፡

ኡጋንዳ በምስራቅ አፍሪካ በግጭቶችን እና ሌሎች አደጋዎችን ሸሽተው የተሰደዱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ስደተኞችን የምታስተናግድ ሀገር መሆኗ ተገልጿል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ያይኔ አበባ ሻምበል
ነሐሴ 19 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.