በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከ 200 በላይ ካርታዎችን ማምከኑን አስታወቀ

የንፋስ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ባለፉት 9 ወራት ብቻ በህገወጥ መንገድ የይዞታ ካርታ አውጥተው የተገኙ ግለሰቦች ካርታቸው እንዲመክን መደረጉን የክፍለ ከተማው የመሬት ማኔጅመንት ሃላፊ አቶ መንግስቱ ተናግረዋል፡፡

ዋና ሃላፊው ከኢትዮ ኤፍ ኤም የቸገረን ነገር መርሃ ግብር ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት በክፍለ ከተማው በርካታ ህገወጥ መንገድ የተሰጡ እና ተመሳስለው የተሰሩ የይዞታ ካርታዎች በመኖራቸው ሰፊ ስራ እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በህገ ወጥ መሬት ወረራ የህገወጥነት መናሃሪያ ተብሎ ስም ሁሉ የተሰጠው ክፍል ከተማ መሆኑን ያነሱት ሃላፊው አዲሱ አስተዳደር በብዛት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ያለው ህገወጥነትን መከላከል ላይ ነው ብለዋል፡፡

ምንም እንኳን አዲሱ መዋቅር ወደ ስልጣን ከመጣ 9 ወራት ያስቆጠረ ቢሆንም አስከ አሁን 200 ህገወጥ የይዞታ ካርታዎች እንዲመክኑ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ህገ ወጥ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታዎቹ ገሚሱ ከቢሮው እውቅና ውጪ ተመሳስሎ የተሰሩ ሲሆኑ ገሚሱ ደግሞ ቢሮው ውስጥ ባሉ የተቋሙ ሰራተኞች የተሰሩ መሆናቸውን በማጣራት ሂደቱ መረጋገጡን ተረጋግጧል ብለዋል፡፡

የይዞታ ካርታዎቹ ህገወጥ መሆናቸውን ያረጋገጥነው ግለሰቦቹ የግንባታ አገልግሎት ፈቃድ ፈልገው ሲመጡ ይዞታው ከእዳ እና እገዳ ነጻ ስለመሆኑ ሲጣራ አልያም በህብረተሰቡ ጥቆማ እንደሆነ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል፡፡

በፎርጅድ ካርታ አገልግሎት ፈልገው መጥተው የተገኙት ግለሰቦችን ለህግ ማቅረባቸውንም ሃላፊው ገልጸዋል፡፡
ቁጥራቸው የማይናቅ ግለሰቦች ካርታ ይዘዋል ነገር ግን ማን ምን ዓይነት ካርታ ይዟል የሚለው ለማጣራት ከህብረተቡ ከሚመጣ ጥቆማ አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ አገልጋዮች እንዲህ ያለ ህገ ወጥ ስራን በማሳለጥ እጃቸው እንዳለበት ያመኑት ሃላፊው አዲሱ አስተዳደር ከመጣ በሃላ ግን ለማተካከል እየሰራ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ምንም እንኳል በዚህ 9 ወራትም በህገ ወጥ መንገድ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ያገኙ ግለሰቦችን ያመከንን ቢሆንም አጣርተን ጨርሰናል ማለት ግን ስላልሆነ ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ብዙ ርቀት በመሄድ ለማስተካከል እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ዳዊት አስታጥቄ
ነሐሴ 20 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.