የአሜሪካ የንግድ ተወካይ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ የፖሊሲ አማካሪ እና ዋና የንግድ ተደራዳሪ ማሞ ምህረቱ ጋር በቨርቸዋል መወያየታቸው ተሰምቷል፡፡

የአሜሪካ የንግድ ተወካዩች ቢሮ በድህረ ገጹ የአሜሪካ የንግድ ተወካይ ካትሪን ታይ ዛሬ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ የፖሊሲ አማካሪ እና ዋና የንግድ ተደራዳሪ ማሞ ምህረቱ ጋር ተነጋግረዋል።

ሁለቱም ሀላፊዎች በአሜሪካ እና በኢትዮጵያ መካከል ስላለው ታሪካዊ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት እና ለተጨማሪ ዕድገት የሚረዳ ውይይት አድርገዋል።

አምባሳደር ታይ ኢትዮጲያ ወደ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎች ያደረገቻቸውን እርምጃዎች ተመልክተዋል፡፡
በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል እየተካሄደ ባለው ግጭት እና የሰብአዊ ቀውስ መድረሱን እና ይህም እንደሚያሳስባቸው ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጲያ በአፈሪካ የእድገት እና እድል (AGOA) ውስጥ የሚኖራትን ሚና ጥያቄ ላይ ይጥለዋል ብለዋል፡፡

አምባሳደር ታይ እና የኢትዮጲያ ተወካዩ በአሜሪካ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የኢኮኖሚ አጋርነት በዘላቂነት ለማስቀጠል በጋራ መስራት አስፈላጊ መሆኑን ተስማምተዋል ሲል የአሜሪካ የንግድ ተወካዩች ቢሮ በድህረ ገጹ አሰነብቧል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ያይኔ አበባ ሻምበል
ነሐሴ 20 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.