ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ የዋንጫ ሽልማት ተሸለሙ፡፡


የውሀ መስኖና ኤነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በዛሬው እለት የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ሽልማቱን ያበረከተላቸው የኢትዮጵያ የታሸገ ውሀ የለስላሳና የአትክልት ፍራፍሬ ማቀነባበርያ አምራቾች ኢንዱስትሪ ማህበር ነው፡፡

ማህበሩ ሽልማቱን ያበረከተላቸው ሚኒስትሩ የህዳሴን ግድብ በተለመከተ ለአለም ማህበረሰብ እያሳዩት ካለው የበሰለ አመራር እና የህዳሴ ግድቡ ሁለተኛ ዙር የውሀ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ በመከናወኑ ነው ተብሏል፡፡

የማህበሩ ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ጌትነት በላይ እንደተናገሩት፣በፀጥታው ምክር ቤት የኢትዮጵያን አቋም እውቀት በታከለበት መንገድ የህዳሴ ግድቡን በተመለከተ ያንጸባረቁት እና ያደረጉት ንግግር በታሪክ መዝገብ መቀመጥ የሚችል ነው ብለዋል፡፡

አሁን ላይ የህዳሴ ግድብ አጠቃላይ ግንባታ 80 ከመቶ መድረሱ የተነገረ ሲሆን
የግድቡ ግንባታ የሲቪል ሥራዎች አፈጻጸም ደግሞ 91 በመቶ ደርሷል ተብሏል።

በሄኖክ ወ/ገብርኤል
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *