ህንድ ኢትዮጵያ ሁሉንም አቀፍ ድጋፍ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ትፈልጋለች ብላለች


በተባበሩት መንግስታት የሕንድ ቋሚ ተወካይ ቲኤስ ቲሩሙርቲ በአፍሪካ ሰላምና ደህንነት ላይ ባተኮረው የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እንደተናገሩት “ከተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ዕርዳታ መርሆዎች ጋር የሚጣጣሙ ጥረቶችን ማፋጠን ተገቢ እና አስቸኳይ ነው ”ብለው።

“ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ትሻለች ”ሲሉም አክለዋል፡፡

የዚህ ሁሉ መነሻ ህውሓት በወታደራዊ ካምፕ ላይ ጥቃት ከሰነዘረ በኋላ ያሉት ተወካይ ይህ አልበቃ ብሎ ወታደራዊ ዘመቻ በመንግስት ላይ ከፍቷል ኤርትራም አዲስ አበባን ለመርዳት ወታደሮቿን ልካለች ነው ያሉት።

“የኢትዮጵያ መንግሥት ያወጀው የአንድ ወገን የተኩስ አቁም ስምምነት አስፈላጊ እርምጃ ነበር እንደ አለመታደል ሆኖ በተኩስ አቁም የተገኘው ዕድል በአንድ ወገን ጠበኝነት ምክንያት አሁን ከትግራይ ክልል አልፎ ግጭቱ ሌሎች አካባቢዎችን እየለበለበ ነው ”ብለዋል።

በተጨማሪም ቲሩሙርቲ ታጣቂ ቡድኖች ሕፃናትን ጨምሮ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የፈጸሙትን ግፍ አጥብቀው አውግዘዋል።

“በትግራይ ለተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እና የወሲብ ጥቃቶች ተጠያቂዎች በህግ ሊጠየቁ ይገባል” ሲሉ የህንድ መልዕክተኛ ተናግረዋል።

ለግጭቱ መፍትሄ በኢትዮጵያ መሪ እና በኢትዮጵያ ሕገ-መንግስታዊ ማዕቀፍ ውስጥ መሆን አለበት ብለዋል። ለዘላቂ ሰላምና መረጋጋት የጋራ መተማመንን ለማምጣት ውይይት እና እርቅ አስፈላጊነት የጎላ መሆኑን አንስተዋል፡፡

መጨረሻም ቲሩሙቲ ህንድ ለኢትዩጵያ አንድነት መጠናከር ያላቸውን ጠንካራ ቁርጠኝነት ደግመዋል።

የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ፣ ነፃነት እና የግዛት አንድነት ለማስከበርም እየተወሰደ ያለው እርምጃ ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁሉ አቀፍ እገዛ ያስፈልገዋል ነው ያሉት ሲል አኒኒውስ ዘግቧል ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ነሐሴ 21 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.