ኢትዮጵያ ነጻነቷን እና ሉአላዊነቷን ለማስጠበቅ በምታደርገው የህልውና ዘመቻ እየደረሰባት ያለውን የውጭ ጣልቃ ገብነት እንደማይቀበሉት የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ተናግረዋል።

ሳልቫ ኪር ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጋር በትላንትና እለት ከተወያዩ በኋላ ህወሃት እያደረሰ ያለውን ጥቃት ኮንነዋል ብለዋል የጠቅላይ ሚኒስትር የፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ተናግረዋል።

“የጉብኝቱ ትኩረት ቁልፍ በሆኑ የሁለትዮሽ እና የክልል ጉዳዮች ላይ በጋራ መነጋገር ነበር” ሲሉም አክለዋል፡፡

ኪር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቢትሪስ ዋኒ-ኖህን ጨምሮ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው የልዑካን ቡድን ጉብኝት ላይ “በተለይ ትኩረት የሰጠው ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችን እና የጋራ የመሠረተ ልማት ግንባታን ማጠናከር ነበር” ማለታቸውን ሱዳን ፖስት ዘግቧል፡፡

አሸባሪውን ህወሃትን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ጎን እንቆማለን ያሉት ፕሬዝዳንቱ በሰኔ ወር የተከናወነው ሀገራዊ ምርጫ በስኬት መጠናቁንና በአባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በተመለከተም እንኳን ደስ አለዎት ሰሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ነሐሴ 21 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *