የብራዚሉ ፕሬዝደንት ጃይር ቦልሶናሮ የወደፊት እጣዬ መገደል ፣መታሰር አሊያም ማሸነፈ ነው ሲሉ ተንብየዋል

የብራዚሉ ፕሬዝደንት ጃይር ቦልሶናሮ ከፊት ያለው ዘመኔ ከመገደል፣ አሊያም ከመታሠር ወይም ደግሞ ከማሸነፍ የሚያልፍ አይደልም ሲሉ ትንቢት ተናግረዋል።

የቀኝ ዘመሙ የብራዚል ፕሬዝደንት ቦልሶናሮ በሚቀጥለው ዓመት ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ያደርጋሉ።
ፕሬዝደንቱ ከግራ ዘመሙ ተቀናቃኛቸው የቀድሞው ፕሬዝደንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ ከባድ ፉክክር ይጠብቃቸዋል።

ቦልሶናሮ በወንጌላውያን መሪዎች ስብሰባ ላይ በሰጡት አስተያየት “ለወደፊት ሕይወቴ ሦስት አማራጮች አሉኝ መታሰር ፣ መገደል ወይም ማሸነፍ” ብለዋል።

በኋላ ላይ የመጀመሪያው አማራጭ “በምድር ላይ ማንም አያስፈራኝም” ከሚለው ጥያቄ ውጭ ነው ብለዋል።

ተቺዎች ግን ቦልሶናሮ ለሳምንታት በሚዘልቀው በብራዚል በ2022ቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የኤሌክትሮኒክስ የድምፅ አሰጣጥ ስርዓት ላይ ጥርጣሬን ለመዝራት የዶናልድ ትራምፕን የመሰለ ዘመቻ እያካሄዱ ነው ሲሉ ተችተዋል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል ።

በኤሌክትሮኒክ የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ለማጭበርበር የተጋለጡ መሆናቸውን ያለ ማስረጃ ሲከሱ ቁይተዋል ይህ ጥያቄ በብራዚል ዳኞች እና በሌሎች ባለሙያዎች ውድቅ ተደርጓል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ያይኔ አበባ ሻምበል
ነሐሴ 24 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *